ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
******ነሐሴ 20/2013******
   ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በደሴና በኮምቦልቻ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የተደረገው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አፀደ ተፈራ ባደረጉት የድጋፍ ጥሪ ሲሆን ጂንካ ዩኒቨርሲቲም ችግሩ የጋራችን ነው በማለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር) እና የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር አለሙ አይላቴ ቦታው ድረስ በመሄድ ቁሳቁሶችን ያስረከቡ ሲሆን “ይህን ችግር መላው የሀገራችን ህዝብ ይመለከተኛል በሚል ስሜት ሊደጋገፍና ትብብሩን ሊያጠናክር ይገባል” ሲሉ ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ ለሚድያ አካላት በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ አብራርተዋል።
      ዶ/ር አፀደም “ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንደሌሎቹ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪያችንን ተቀብላችሁ ከአንድ ሺህ ኪ.ሜ በላይ አቋርጣችሁ መታችሁ ወገናችሁን ለመርዳት መምጣታችሁ ከድጋፉ በተጨማሪ ለተፈናቃዮችም ትልቅ ሞራል ይፈጥራል” በማለት በወሎ ዩኒቨርሲቲና በደሴ ህዝብ ስም ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴና የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አለሙ ወደ 1.5 ሚልየን ገደማ ወጪ የተደረገባቸው የድጋፍ ቁሳቁሶችን አስረክበው በመጨረሻም ተፈናቃዮችን ከፊል ወደ ተጠለሉበት ሳይት በመሄድ ጎብኝተዋል።
                                          “Knowledge for Change”