የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ አሞ ዞን የጂንካ ማረሚያ ተቋምን ጨምሮ በዞኑ ለሚገኙ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በተለያዩ ጊዜያት የኮምፒዉተር ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ሰሞኑን ደግሞ በዞኑ በየደረጃው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን በድጋፍ መልክ አስረክቧል፡፡ በዚሁ መሰረት ለዞን ማዕከል ሴክተሮች 65 ኮምፒውተሮቸ፣ጂንካ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ለ10 ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ኮምፒውተሮችን አስረክቧል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እያደረገው ያለው ይህ ድጋፍ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመለት ዓለማዎች አንዱ በመሆኑ በስኬቱ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ የምትደሰቱት እኛንም የሚያስደስተንና የሚያነሳሳን ተግባር ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ዪንቲሶ ኮምፒውተሮቹ ለእያንዳንዳቸው ፕሪንተር እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም አገልግሎቱን ያገኘው ማህበረሰብና አገልግሎት ሰጪው እሰከሚረካ ይህ በጎ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ፐሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
// እውቀት ለለውጥ!! //