የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሀረጋዊያንና አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ የምግብ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከተ

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በጂንካ ከተማና ዙሪያዋ ለሚኖሩ ሀረጋዊያንና አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ680 ሺህ በላይ ወጪ የሆነባቸው የምግብ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከተ
የጂንካ ዩኒቭርሲቲ በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች በኮቪድ-19 እና በኮሌራ ወረርሽኝ ለተጠቁ የማህበረሰብ ክፍሎች የመድኃኒትና የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ይህ በእንዲህ እያለ ሰሞኑ በጂንካ ከተማና ዙሪያዋ ለሚገኙ 5 መቶ ለሚሆኑ ሀረጋዊያንና አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 30 ኪ/ግ የምግብ ቁሳቁሶችና ሁለት ሁለት ሊትር የምግብ ዘይት አበርክቷል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እያደረገው ባለው ድጋፍ በጣም ደስተኛ እንደሆነና ይህ ደግሞ የማዕድ እናጋራ አንዱ ተምሳሌት ነው ያሉት የዩንቭርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ዪንቲሶ ድጋፉ የመጀመሪያችንም የመጨረሻችንም ሳይሆን በቀጣይም ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ለማረጋገጥ ድጋፋችንን አጠናክረን የምንቀጥለው ይሆናል ብለዋል፡፡