የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና በፌስቡክ ፔጃችን እንደገለጽነው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓም ነው። የጂንካ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ-ምዕራብ 750 ኪሜ ላይ ትገኛለች። በአውቶብስ የሚትጓዙ በአርባ ምንጭ በኩል አድርጋችሁ ጂንካ ትደርሳላችሁ። መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም ዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎችን ከአርባ ምንጭ ወደ ጂንካ ያጓጉዛል። ወደ ፍቅር መዲናዋ ጂንካ በሰላም ድረሱ! መልካም ጉዞ!

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ