የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአርንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከችግኝ ተከላ ጎን ለጎን በተለያዩ ጊዜያት የተተከሉትን የመንከባከብ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ

ሀገራችን የተያያዘችዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ–ግብር መነሻ በማድረግ የጂንካ ዩኒቨርሲቲም በ21/11/2012 ዓ/ም በአንድ ጀምበር የ1 ሺህ ስድስት መቶ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን በግቢው ዉስጥ ተክሏል፡፡ ቀደም ብሎ በዩኒቨርሲቲው ግቢ በተዘጋጁ ጉድጓዶች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከዞን ማዕከልና ከጂንካ ከተማ አስተዳደር ከመጡ አመራሮች ጋር በመሆን ተግባሩን ፈፅሟል፡፡ የተከናወነዉን የአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ዪንቲሶ አከባቢያችን እንዲያገግም የተtለያዩ ሃገር በቀል ችግኞችን በተለያዩ ጊዜያት ከምንተክላቸው ሀገር በቀልና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ዐፀዋት ጎን ለጎን የተከልናቸዉን ችግኞች በቅርበት በመከታተል መንከባከብ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በዚሁ ቀን ከችግኝ ተከላ መልስ የደም ልገሳ ፕሮግራምም ተካሂዷል፡፡የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በቀሪው ጊዜ ይህንኑ መረሃ-ግብር አጠናክሮ በመቀጠል በግቢዉና በጎርጎቻ ተራራ ስር ባለው ጥብቅ ቦታው ላይ እስከ 10 ሺህ የዛፍ ችግኞችን እንደሚተክልም አስታውቋል፡፡