በድጋሚ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

መስከረም 16/2014
በድጋሚ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሰባት የት/ት ፕሮግራሞች የሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር የምዝገባ ጊዜ እስከ መስከረም 8/2014 ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ደግሞ መስከረም 18/2014 እንደሆነ ማሳወቃችን ይታወሳል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም ምዝገባ የሚካሄደው እስከ መስከረም 30/2014 እንደሆነና የፈተናው ጊዜ ደግሞ በዚሁ የዩኒቨርስቲው የፌስቡክ ገፅ፣ በድረገፅ(www.jku.edu.et) እና በዩኒቨርስቲው ቴሌግራም ቻናል(t.me/JKUPIR) የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልፃለን።
//የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት//