“ምሁራን ሀገርን በመገንባት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል” ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ
* ታህሳስ 24/2015 ዓ.ም*
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምሁራን የምክክር መድረክ ከአጠቃላይ ከዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሰራተኞች እንዲሁም የአስተዳደር ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር እየተካሄደ ነው።
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ማለትም ከታህሳስ 21-22/2015 ከዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ጋር “የምሁራን ሚና በሀገር ግንባታ” በሚል ርዕስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እንደተካሄደ መዘገባችን የሚታወስ ነው።
በዛሬው እለትም(ታህሳስ 24/2015) ከአጠቃላይ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአካደሚክ ቴክኒካል ረዳቶች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር የውይይት መድረኩ እየተካሄደ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ የምክክር መድረኩን አጠቃላይ ይዘትና አላማ በማብራራት መድረኩን ከፍተዋል።
ይህ መድረክ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚካሄድ ሲሆን የምክክር መድረኩን በሰብሳቢነት እየመሩ ያሉት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት በሚኒስቴር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሀላፊ ክቡር አቶ ዛዲግ አብረሃ የውይይት ሰነዱን እያቀረቡ ሲሆን ከዛሬ ታህሳስ 24/2015 ከሰአት በኋላ ጀምሮ እስከ ነገ የጠዋቱ ክፍለጊዜ ድረስ የቡድን ውይይት በማድረግ ከሰአት በኋላ ደግሞ የማጠቃለያ መድረክ እንደሚኖርም ነው የተገለፀው።
ማጠቃለያውን ጨምሮ ሌሎች በምሁራን የሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
የጂ/ዩ የህ/አ/አ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት