የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ቫይረስ ዙሪያ ለማህበረሰቡ የሚሰጠዉን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችንና በመላ ዓለም እየተስፋፋ የመጣው የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የበኩሉን ሃላፊነት ለመወጣት ከሚያደርጋቸው ጥረቶች አንዱ በዞኑ ዉስጥ ባሉ ወረዳዎች የገበያ ቀናትነን ጠብቆ የእጅ ማስታጠብ፣የአፍና አፍንጫ ማስክ አጠቃቀምና በኮቪደ-19 ቫይረስ ዙሪያ ልይ ያተኮረ በራሪ ጽሁፍ የማሰረጨት ፕሮገራመ አንዲሁም በቫይረሱ ስርጭት ለመቀታት በሚደረገው ጥረት ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ የማንቂያ ቅስቀሳ በዞኑ ደቡብ አሪ-ጋዘር፣ሐመር-ዲመካ፣ማሌ-በነታና በና ፀማይ ቀይአፈር ተከናውኗል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሴ/ህ/ወ/ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም ከየወረዳዎቹ የጤና ጽ/ቤት ጋር በመሆን ያከናወናቸዉን በኮረና ቫይረስ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በቀጣይም አገልግሎቱ ባልተዳረሰባቸው ሌሎች ወረዳዎችም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡