ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ተሰጠ

ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ተሰጠ

በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (የአገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራት) የተውጣጣና ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ የሆነ ኮሚቴ በዞኑ ለሰላም፣ ለአብሮነትና ለልማት አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ሰጠ። የዋንጫ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ከተሰጣቸው ውስጥ የጂንካ ዩኒቨርሲቲና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ይገኙበታል። ይህ ዕውቅና የተማሪዎቻችን፣ የመምህራኖቻችንና የአስተዳደር ሰራተኞቻችን ጥረትና ትብብር ውጤት ስለሆነ እንኳን ደስ አለን።