
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኦሞ ዞን የተለያዩ አከባቢዎች አገልግሎቱን ለማስፋፋት ከያዘው ዕቅድ በመነሳት በሰሜን አሪ ወረዳ 20 ሺህ ካ/ሜ ቦታ ለምርምርና ጥናት ማዕከልነት ተረከበ
የጂንካ የኒቨርሲቲ ስራዉን ከጀመረ ጥቂት ዓመታት ቢያስቆጥርም በዚህ አጭር ጊዜ ከመማር ማስተማር ተግባር ጎን ለጎን በተለይ ለማህበረሰቡ ተገቢዉን አገልግሎት በመስጠት ቀላል የማይባሉ ተግባራት እንዳከናወነ አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በሰሜን አሪ-ገሊላ ከተማ ለምርምርና ጥናት ማዕከል አገልግሎት የሚውል 20 ሄክታር መሬት ተረክቧል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ዪንቲሶ በእርክብክቡ ወቅት እንደገለጹት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስካሁን በዞኑ ያከናወናቸው ተግባራት ጅምር እንጂ እንደ ትልቅና የመጨረሻ ደረጃ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡ይልቁንም በቀጣይ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በሰሜን አሪ በተረከብነው ቦታ ማረፊያ ግንባታ ገንብተን ተማሪዎቻችንና መምህራንን በመላክ ማህበረሱቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ እንሰራለን ያሉት ፕሮፌሰር ገብሬ ዪንቲሶ መሰል ተግባር በቀሩትም ወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
//ዕውቀት ለለውጥ!!//