የአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል

የተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሰላም ደርሰዋል። ነባር ተማሪዎች፣ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ፣ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም የጎርጎቻ 1ኛ ደረጃ፣ የሚለኒዬም 2ኛ ደረጃ፣ የጂንካ 2ኛ ደረጃና የመለስ ዜናዊ መሰናዶ ት/ቤቶች ተማሪዎች መንገድ ዳር ተሰልፈው ጠብቀው በፍቅር ተቀብለዋቸዋል። ዩኒቨርሲቲው 22 አውቶብሶችን ከተቀባይ ቡድን ጋር አርባ ምንጭ በመላክ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም በርካታ ተማሪዎችን ያጓጓዘ ሲሆን ሌሎች (የቀደሙና የዘገዩ) በራሳቸው ወጪ መጥተዋል። ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ፤ እንወዳችሗለን።