ተማሪዎች እንኳን በሰላም ተመለሳችሁ!

የተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች ከትናንት መስከረም 22 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ ወደ ግቢ በመግባት ላይ ይገኛሉ። በዩኒቨርሲቲው፣ በጂንካ ከተማና በደቡብ ኦሞ ዞን ማህበረሰብ ስም ወደቤታችሁና የፍቅር መዲናዋ ጂንካ እንኳን በሰላም ተመለሳችሁ እንላለን። ዘንድሮ የበኩር ተማሪዎቻችን በታላቅ በዓል ይመረቃሉ። ሌሎችም በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች ይኖሩናል። ዓመቱ እንደ ወትሮው በሰላምና በውጤት እንድያልቅ ሁላችንም ዘብ በመቆም ተቆርቋሪ መስለው በመቅረብ የጥፋት ተልዕኮ ለማሳካት የሚሞክሩ ካሉ ማጋለጥ አለብን።
ዕውቀት ለለውጥ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ